https://andro.io/app/ahmaric-quran
Power 100
Android app profile
የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም በድምፅ (Minbertv) for Android – Latest Version & Features
by sysol tech
★★★★★
(0 ratings)
Rate this app
How do you feel about የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም በድምፅ (Minbertv)?
Thanks for your feedback!
> 2.2k
Monthly Downloads
~$900
Estimated Cost
Screenshots
About የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም በድምፅ (Minbertv)
ከሃምሳ ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና በሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ እንሆ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል። የድምፅ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በዚህ መተግበሪያ እስኪጫን ድረስ፤ ለጊዜው ሱረት አል ፋቲሃን ጨምሮ ከሱረቱ አን ናስ እስከ ሱረቱ አን ነበእ (አንድ ጁዝ) የትርጉም ድምፅ ሥራው ያለክፍያ ቀርቧል።በዚህ አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን የጠራ ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ሰዎች ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። በመኾኑም ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ሂደት ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።ይህን ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት እስከ ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። እኛንም በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!!